

| ፌዴሬሽኑ በ30ኛው የለንደን ኦሎምፒክ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ይፋ ማድረግ ጀመረ |
|
|
|
| እሮብ, 29 የካቲት 2012 16:52 |
|
በዚህም መሰረት በ2012 ዓ.ም በተደረጉ ውድድሮች ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት አማካይነት በስልጠናው ሁለተኛ ዙር ላይ ለማራቶን የተመረጡ አትሌቶችን ዝርዝር የካቲት 21/2004 ዓ.ም ይፋ አድረጓል፡፡ አትሌቶቹ የተመረጡት ደግሞ በ2012 በተካሄደው ኢንተርናሽናል የማራቶን ውድድሮች ተሳትፈው ባስመዘገቡት ፈጣን ሰዓት መሆኑም ተገልጿል፡፡
ይፋ የተደረጉት አትሌቶች ስም ዝርዝር በወንዶች 1.አየለ አብሽሮ 2.ማርቆስ ገነቲ 3.ዲኖ ሰፍር 4.ታደለ ቶላ በሴቶች 1.አሰለፈች መርጋ 3.ብዙነሽ በቀለ 2.ማሬ ዲባባ 4.አበሩ ከበደ
ሲሆኑ በውጤታቸው ከተመረጡት ከነዚህ አትሌቶች የተሻለ ሰዓት የሚያስመዘግቡ አትሌቶች ከመጡ ደግሞ በቀጥታ በቡድን ውስጥ የሚካተቱ ይሆናሉ፡፡ ከሚያዝያ ወር 2004 ዓ.ም በኋላ ደግሞ አግባብነት ባላቸወ የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተሳትፈው በጣም ጥሩ የሚባል ውጤት ያስመዘገቡ ሁለት ፣ሁለት አትሌቶች ከሁለቱም ፆታ የሚመረጡና የሚቀላቀሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲሁም የመካከለኛና የረዝም ርቀት ተሳታፊዎች በ3ኛው ፌዝ በሚደረግ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ይፋ እንደሚሆኑ ፌዴሬሽኑ ጨምሮ አመልክቷል፡፡
ምንጭ፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን |
| Last Updated on እሮብ, 29 የካቲት 2012 17:03 |


Copyright©2011-ETHIOPIAN RADIO AND TELEVISION AGENCY (ERTA).
All Rights Reserved!
Designed and Developed by: ERTA-MEDIA TECHNOLOGY-ICT-DEPARTMENT OF-SOFTWARE DEVELOPMENT.






